Monday, June 29, 2009

The new Habesha line.

I guess the word new is relative. But after a weekend of dily daly, trying to check out the phoneline i got from my co-worker and oh my my.....
It was kind of rude awakening to hear that how many people have ample time to trash out one another. 75-80 percent in my view were some how "i missed the right turn and up here so let me out types." Didn't leave immediately, rather i stayed and tune in for whatever is on the menu. Half an hour later shoked and surprized left the line. For the next two three days keep coming start to enjoy whatever hopping from line to line. Came accross through different caracters not all of them were shoking but somehow.....Ooooooooo Weeeeeeeeeeeeee.
One of these days i will start posting my observations on weekly or dayly basis. For now check you later.

The king has moved on.

A sad day for our planet. I was at work while hearing this crushing news Michael Jackson has gone. For me or all the fans The great MJ is in our hearts.He will live forever. He was our God's gift. He is super nature, pure spirit and full of love.


He awaken our eyes to the beauty of nature, the urge to listen through the heart and flow with the beautiful music.He did everything to make us feel his love and God's presense. While devastated i over heard someone saying "Michael Jackson has nothing to proof to the world. He has finished his job on earth and moved on." Seems hard for the fans but it has some truth in it. Let's think about all MJ's songs and artistic performance.He has changed us for the better beyond all human made barriers, color, race, culture and what have you.He was the greatest yester day, He is the Great one today and He will be the Greatest for Eternity.


MAY HIS SOUL REST IN PEACE

Friday, June 12, 2009

11


ህይወት ክፍል 11


የሰው ልጅ በኖረባቸው ብዙ ሺኅ ዓመታት በተፈጥሮ ያደረገው ዝግመታዊ ለውጥና ከተፈጥሮ ጋር ባደረገው ፍጥጫ የደረሰባቸው የቴክኖሎጂ ውጪቶች የሚያስደንቁን ቢንም እንዳንድ ጊዜ ገን ግራ እያጋቡን ይጋኛሉ፡፡



ከቻርሊስ ዳር ዊን ቴዎሪ ተነስተን የሰውን ልጅ በራሱ ላይ በተፈጥሮ ክስተቶች በመታገዝ ያደረገውን ዝግመት ለውጥ ሰናይ በማህበረሰብ በመሰባሰበብ ያሳለፈውን ህይወትና የማህበረሰቡን የዕድገት ደረጃ እንደናጢን መገደዳችን አሌ አይባልም፡፡



በኢትዮጵያችን እንኳ ባሪያ መሸጥ መለወጥ እንዲቆም በአዋጅ ደረጃ /በተገበር ላይ ከአዋጁ በኋላም ቆቶ ተሰተዋሏልና፡፡/ በአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ነው የተደረገገው፡፡ /ይህ የባሪያ ፍንግሌ ግን በዘመናዊ መልክ ቀጥሎ የመኖር እስትንፋሱ በተወሰነ ደረጃ ቀይሮ ባሪያ የነበረው ሠራተኛ ተሰጥቶ ይገኛል፡፡/ እዚህ ላይ አማረኛ ቋንቋ ስሚችግረኝ ለቃላት አጠቃቀሜ እንባቢን ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡/



በቴክኖሎጂና ብሔራዊ ሀብት መጠን በልፀገዋል በሚባሉት ሀገሮች ሁሉ የባሪያ ፍንግሌ /ያላችሁትን በሉኝ እንጂ/ እንደቀጠለ ነው ያለው፡፡ እዚህ ላይ ምሳሌ ብጠቅስ ሃሳቤን ግልፅ ያደርገዋልና እንካችሁ፡፡



ለሞኑን የዓለም ዋንጫ እተካሄደ ነው፡፡ እኔ እንኳን ጥሩ የእግር ኳስ ጥበብ ለማየት ብቻ ሰምቼ እያለሁ እንጂ በቀን በቀን የአንቀጽ ልፍ ሰዓቱን እንዲሻብብቅ አልፈልግም፡፡ ወደ ቁም ነገሩ ልግባና የአንዱ ክለብ የእግር ኳስ ጨዋታ ሙያጠኛ /ፐሮፌሽናል የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃለ ከተካልኝ/ በኮንስትራት ለተወሰነ ዓመት ከተሸጠበት ክለብ ወደ ሌላ ክለብ ተመልሶ ሲሸጥ ይሰተዋላል፡፡ ተጫዋቹም ብዙ አያሳስባውም፡፡ ገንዘብ እስከተከፈለው ድረስ የሚሸጠው ክለብ አተረፈበት አላተረፈበትም፣ ለብዕናው ወደ ሸቀጥነት /ዘመና ባሪያነት/ መለወጡ ደንታዎ አይሰጠው፡፡ እንግዲህ ይህ ሁኔታ ህይወትን በማቆየት ውሳኜ ደረጃ ይለያይ እንጂ ከጥንቁ የባሪያ ፍንገላ በምን ይለይ? የተሸጠ ተጨዋች ደገሞ ጨዋታው ከተቀነሰ ምንም ያህል ለክለቡ ውለታ የዋለ ቢሆን እንደ አሮጌ ቆርቆሮ መጣሉ አይቀሬ ነው፡፡ እርገትጥ በቁሳዊ ጥሪት መያዙና የባንክ ደብተሩ ላይ ቁጥሮች መነበባቸው ከሥጋዊ ምቾት ትንሽ ይጠቀመው ይሆናል፡፡ ነገር ገን ለሞራል ጎዳቱና ለህሊናዊ ጥያቄ ምን መልስ ይገኝለታል?



ሃሳቤን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ አንድ ሌላ ምሳሌ ልጨምር፡፡ አኔሁ በለፀጉ የሚባሉ አገሮች ብዙ የተማረ ኃይል እንዳላቸው ይነገራል፡፡ የተማረውን ኃይል እንዴት አፈሩት ብንል ገን የሚኖረን መልስ በየሀገሩ ጥሩ ጭንቅላት ያለውን ምሁርን በተለያየ ዘዴ በማስኮብለል እያስቀሩት መሆኑን ደግሞ የተደበቀ ሁኔታ አለመሆኑን እንረዳለን፡፡



አነኝህ ምሁራን የሚኩበልሉበት ምክንያት ቢለያይም ከሀገር ወጪሄደው ቢሮሩ ገን በቁጭት እየተብሰለሰሉ አወዳደቃቸው እንደማያምር ይደመጣል፡፡ የቤተሰብ ናፍቆት፣ የሀገር ውበትና አየር፣ የደርጉበት ሰፈርና ጎደኖች፣ የተማሩበት /ቤና የልጅነት ፍቅረ በሃሳባቸው እየተመላለሰ ጤና እንደሚነሳቸው ከኖረበት /ሀገር ወደ ሌላ በሥራም ሆነ በዕረፍት ለሄደ ሰው የሚረስ ነገር ስሆነ አዚህ ላይ ብዙ ማለት የሚስፈልግ አይመስለኝምም፡ አስገዳጅ ሁኔታዎችም እንደሚኖሩ አልዘነጋውም፡፡ ነገር ገን ለሰው ልጅ መብት ተከራካሪዎች ነን እያ በየመገናኘው ብዙሃን ባሸበረቁ ቃላቶች ዲማጉጋቸውን የሚለፍፉ ሀገሮች ከአንድ ወቅተ ጀምረው በሚያወግዙበት አፈቸው በየጊዜው በሚፈጠሩት ገደብ የለሽ ምንክያቶቻቸው በማደግ ላይ ያሉ አገሮን ምርት ዜጎች እየሸበቡ በዘማነው ባርነት ማድከማቸውና መጠፈራቸው የጥንተ ባርነት መልኩን ለውጦ እስከ ዘመናችን ድረሰ አልዘለቀም ለማለት የምንደፍር ሰንቶቻችን ነን? በአሜሪካ የጠፈር ምርምር ማዕከል ሆነ የመክላከያ ኃይል ተቋም በእውቀታቸው ተከብረው የሚሰሩ ምሁራን በራሳቸው ፍላጎት መልቀቅ ቢፈልጉ የመኖራቸው ዋስትና አደጋ ላይ መውደቁን ማሰብ ራሰ ጥንት በባርነት ከማቀቁ ሰዎች ልዩነቱ ምን ያህል የሰፋ ነው?



ከላይ ለመጠቃቀስ የሞከርኩት የሰው ልጅ ተፈጥሮን ለመለወጥ ባደረገው ትግል ብዙ ቢሳካለትም በራሱ የአስተሳሰብ አድማስ ነው ያደርገው ለውጥ ግን ሰው ሆኖ ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙም ፈቅ አላለም ለማለት ነው፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?


9


ህይወት? ክፍል 9
ብዙነሽ ወደ ቢሮ ስተወጣ ግቢዋን የሚጠበቅላት ላስቻለው የተባለውን ከትንሽነቱ ያሳደገችውን ውሻ ዘወትር እንደምታደርገው ደባብሰው እንገቱ ላይ ካለው ቀርቶ ጋር የታሰረበትን ሰንሰለት አላቀቀችለት፡፡ ላስቻለው እየፈነደቀ ግቢን አንዴ ከዞረ በኋላ ተመልሶ መጥቶ እግሯን ስር ተጋደመ፡፡ ዓይኗ እንባ አቅርሮ … መተኪያ… ብላ በቀስታ ተናግራ የግቡዋን በር ዘግታ ውጣች፡፡

ቢሮ አስከትደርስ የምታስላስለው የጓደኛዋ አስቴር ስለተላከላት የልደት ቀን ጥሪ ወረቀት ነበር፡፡ አስቴር ጋር ተኳርፈው ከተላያዩ ሦስት አመታቸውን ይዘዋል፡፡ አብሮ አደግ ጓደኛዋ ጋር የተከራረፈበት ጉዳይ ቀላል ቢሆንም ጥፋቱ የሷ ስላልሆነ በጣም አምርራ ተለይታታለች እየዋለ ሲያድር አስቴር ጥፋቷ ስለገባት በሰበቡም ይቅርታን ለማግኝት ሁለት ጊዜ በየዓመት የልደት በአሏ ላይ እንድተገኝላት ብትጠራትም ብዙነሽ … ካሁን ወዲህ ሰው ለምኔ… በማለት አልተበገረችላትም፡፡

…ላስቻለው… በሚል ስያሜ የምጠራውን ውሻም በህጻንነቱ ማሳደግ የጀመረችው ከምትወዳት ጎከኛዋ ጋር ተኮራርፋ ስተለያይ ሲሆን ለውሻው በግል …መተኪያ… ትለዋለች፡፡ የአብሮ አደግና የሚወዱት ጎደኛን ማስረሻ ለማሰለት፡፡

አብሮ አደግ ጓደኛዋ አስቴር አሁንም ሳትሰለች ለሦስተኛ ጊዜ በላከችላት የጥሪ ወረቀት በአጥሩ የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት በማንሳት ይህንን ሶስት ዓመት ልቧ እያለቀሰ እንደተሰቃየችና ለመጨረሻ ጊዜ ጥሪውን እንደላከችላት የሚገልፅ የማስጠንቀቂያ ጽሁፍ ከግርጌው ሰፍሯል፡፡

በቢሮው የክፍል ኃለፊነቷ ብዙነሽ በቀልጣፋነቷ የተመሰገነች ቢሆንም በዛሬው ቀን በምትሰራው ሁሉ ነገር ላይ ፊቷ የኃዘን ደባብ እየተበበበትና እንዳንድ ጊዜም ትናንሽ ነገር ሁሉ እየረሳች ፀሐፊዋ ለአንድ ጉዳይ ሁለት ጊዜ መሳሳቷን ነግራታለች ከዚህ በኋላ ነበር ፀሐፊዋም ብዙነሽ ሰዎች አንዳይረብሿት ባለጉዳዮችን ለሌላ ጊዜ እየቀጠረች ያሰናበተቻቸው፡፡

ምሳ መድረሻ አካባቢ ስልክ ተደወለላት ከሃሳብ ማጥ ውስጥ አስበርግጎ ስወጣት ስልኩን ገላምጣው በንዴት ብድግ አደረገችው፡፡ ታዲዋስ ነው ከውሻዋ ቀጥሎ የምትወደው የወንድ ጎደኛዋ፡፡

ለምሳ ወጥቶ እንዲስዳት ከነገረቸው ሀኋላ ስልኩን በመዝጋት የሚደላው ወንበር ላይ ተደግፋ በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ የቢሮ ጠረጴዛዋ ላይ በስጦታ ወረቀት ተጠቅልሎ ገብ ያለውን ናሽናል ፓናሶኒክ የሙዚቃ ማጫወቻ ቀኝ ላይ ዓይኗ ሲያርፍ ከሶስት ዓመት በፊት ስለተከሰተው ሁኔታ በትዝታ አስታውሰ ቁጭት ያበስላስላት ገባ፡፡

ያልተነጠፈው አልጋ ላይ ጋደም ብላ አስቴር ያዋስቻት ትንሽ ቴፕ የሚያንቆረቁረውን …አይ አዎ በሶሌንግ… የሚለወን የሮድ ስቴዋርት ዘፈን እያዳመጠች፡፡ ያልተነጠፈው አልጋ ስላልተመቻት ብድግ በማለት የአልጋ ልብስ፣ ብርድ ልብስ አንሶላ አነሳስታ ማንጠፍ ጀምራ ሳትጨርስ ከአልጋው አጠገብ በተቀመጠው ኮሜዲኖ ላይ ያለችው ትንሽ ቴፕ በብርድ ልብሱ አማካኝነት የሲሚንቶው ወለል ላይ ውብላ ወድቃ ብትንቅኗ ወጣ፡፡ ብዙነሽም ደነገጠች እየቆየችም ስትሄድ ደግሞ አይኗ ቲማቲም እስኪመስል አነባች፡፡ አስቴር ከወንድ ጎደኛዋ በስታ ያገኝቻትና የምትወዳት ቴፕ ነበረች፡፡ ብዙነሽ ለቅሶዋን ሳትጨርስ ለጎደኛዋ የቴፑን መርዶ በስልክ ስታደዳት አስቴር …በፍቅር ህይወቴ መጣሽብኝ ካሁን አንተዋወቅም አትድረሽብኝ… ነበር ያለቻት፡፡ ብዙነሽ ስልጁን ቀስ ብላ ዘግታ ስታስበው መናደዱን ተያያዘቸው፡፡

የቢሮው በር ተንኳክቶ ፀሐፊዋ የምሳ ሠዓት መድረሱን ስታበስራት ነበር ከትዝታዋ የተመለሰችው ብዙነሽ ለፀሐፊዋ መልሰካም የእረፈት ቀን ተመኝታላት በአንድ እጇን የስጦታውን ፓኬት በሌላው ቦርሳዋን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጋ ስትወጣ ፀሐፊዋ ፓኬቱን ልትረዳት እንደምትችል ብታስታውሳትም ግድ የልመ… የሚል ሰጥታች በችኮላ ተንደረዳረች፡፡ የመ/ቤቷን የውጪ በር እንደወጣች ታዲዎስን አመኪናው ውስጥ እንደተቀመጠ አየችው መኪናው ጋር ደርሳ በሩን ከፍታ እንደገባች በልቧ የመነኩሰች ልዕልቴ ሰላምታዬ ይድረስሽ… በማለት ሳም አደረጋትና ጭኗ ላይ ያለውን የስጦታ ዕቃ ተመልከቶ መኪናውን አንቀሳቀሰው፡፡

ሆቴል ግብተው መሳ ቀርቦላቸው ሁሉ ዝምታ ሰፍኗል በመሃላቸው፡፡ ከምሳ በኋለ ቡና እየጠጡ ሳለ … በመጨረሻ ልታረቃት ወሰንኩ… አለችው ብዙነሽ የቡናውን ስኒ ማስቀመጫው ላይ እንዳለ አያሸከረከረች፡፡

ታዲዎ ብዙ ጊዜ ስለአብሮ አደግ ጎደኛዋ አጫውታዋለች፡፡ ስለ አስቴር አውርታ አትጠግብም፡፡ ነገር ገን ሁሉት ዓመት ሜሎ ልደታ ላይ እንድትገኝ ስትጠራት ወሳኔዋ ቁጥር ነበር፡፡ በአስቴር የልደት ቀን ግን ብዙነሽ ስታለቅስ ነው ያሳለፈችው፡፡ የዘንድሮውን ግን ልትሄድ ወሰናለች፡፡ የስጦታ ዕቃዎ አዘጋጅታላታለች፡፡

…ግሩም ነው… …በዛሬ ታላቃ ቀን ገን እኔም ብገኝ ምንኛ ደስ ባለኝ እነዚያ ጅቦች አስችኳይ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡… አለና ሲና ደድ እንደያደርገው እጅን አወናጨፈ ‹ጅቾች› የሚላቸው አለቆቹን ነው፡፡

…በታክሲ ልሄድነው እንዴ ታዲያ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ነውኮ ጥሪው?... አፈጠጠችበት

የገንዘብ ቦርሳውን አወጥቶሄሳቡን ጠረጴዛው ላይ ካኖረ በኋላ ከመቀመጫው እየተነሳ …አንቺ መ/ቤት ታደርሺኝና መኪናዋን ይዘሽ ትሄዳለሽ፡፡ አላት ትከሻዋ ላይ እጁን ጣል አድርጎጎ፡

…ዛሬ እንኳን መሪ ባልይዝ ይሻል ነበር፡፡ ቸግር ከሆነ ግን ምን ይደረግ፡፡… በማለት የመኪናወውን ቁልፍ ተቀበላ በሹፊሩ መግቢ በኩል ገብታ ለሱም በሩን ከፍተችለት፡፡

መ/ቤቱ አድርሳው ቶሎ ከጨረሰ ከቤቷ እንዲጠብቃት ከነገረችው በኋላ …መተኪያ… ለምትለው ውሻዋ የአሁድ ቀለቡን ከተኮናተረችለት ቦታ በመያዝ ውሻዋን ለማየትና ከዚያም ልብስ ለመቀየር ወደ ቤቷ ከነፈች፡፡

ቤቷ በር ላይ ደርሳ መኪናዋን እንደቆመች የተሰበሰቡት ሰዎ ሲጠቃቀሱባት አስተውላ ነበር እንዳለ ገባት፡፡ ሁለት ፖሊሶች ወደ እሷ ተጠግታው ሰላምታ ሰጥተዋት ለምርመራ እንደሚልጓት ነገረው ፖሊስ ጣቢ ወሰዷት፡፡ ለጥያቄ ስምንት ሰዓት የሄደች …ስልክ እንኳን ልደውል፡፡… እባካችሁ አድራሻዬን እንኳ ለዘመድ ንገሩል …እያለች ብትወተወትም ለጥያቄዋ መልስ ያገኝቸውና በዋሰ የተፈታቸው ከጠዋቱ በሦስት ነው፡፡ የታሰረችበት ምክንያት ያትም ውሻዋ …መተኪያ… ኳስ ሊያወጣ በአጥር ዘሎ ግቢዋ የገባውን የጎረቤት ጎረምሳ ስለነከሰ ነበር፡፡ቀን የጠፋን በሬና የሚሰርቅ ሌባን ያገናኛል፡፡.. እንዲሉ፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?

8


ህይወት? ክፍል 8
ዘመን ዘመንን እየተካ ሲሄድ ትውልዱም እንዲሁ ተክቶ ማለፍ አይቀሬ ነው ከዘመን ጋር አብረው የሚስወጡተፈጥሮዊም ሆኑ ማህበራዊ ክስተቶች በየትውልዱ ላይ ከሚያትሙት አሻራ ለቀጣዩ ትውልዱ ስብዕና ወሳኝነት አላቸው፡፡

ከአያቶችን ዘመን ስንነሳ ሰዎች በየተሰማሩበት መስክ ለፍተው ደክበመው የተገኝውን እነሱም በዛ ከቤተሰብ ተከፍለው፣ ከሥራ ውጪም ከዕድአኩዮቻቸው ጋር ፀጋቸውን አውግተው /ለልማት ሥልም ሆነ ለሽምግናል/ አደባባይ ውለው አመሻሽተው ይገባሉሉ፡

የነሱ ልጆ /የኛ ወላጆች ማለት ነው፡፡/ ከብት አያገዱ ወይንም ሌላ ስራ እየሰሩ የልጅነት ጨዋታችውን ከጓደኖቻቸው ጋር ተዋዘተው አሳልፈውታል፡፡ ከፍ እያሉም ሲሄድ የቤተ ህክነት የትመህርተን ቀስመው አሌም የቤተሰቢቻቸው ዱካ ተከትለው ከጠነከሩ በኋለ በየስራ መስኩ ተስርተዋል፡፡ ገበሬውም ወደ እርሻው፣ ነጋዴውም ወደ ንግዱ፣ ወደ ወትድርና ወደ እጅጥበብና ሌላም ሌላም ሙያዎች ላይ በመሰማራት ቤተሰብ መስርተው እናነ ተክተዋል፡፡

የድሮ ሰው ኩራቱ ተተኪ ልጅ ማፍራተቱ ነው ይባላል፡፡ … ተተኪልጅ… ታዲያ በዘመኑ የነበሩ የራሱ መስፈሪያ ነበረው፡፡ እግዚአብሔርን ፈሪ፣ ሰውን አክባሪ፣ ወላጆቱን ጧሪ የሚሉት ሐረጎች ከነበሩት መመሪያዎች ይደመራሉሉ፡

እናም እንግዲ ት/ቤት ገብተን፣ከዚህም ሥራ ላይ በመሰማራት እየተፈጨረጨርን ሲሆን ዘመናችን ግግ በብዛው መልኩ በቴክኖሎጂ እየታገዘ ወላጆቻችን ከኖሩበት ይልቅ ኑሮን የተቃለለ አድርጎልናል፡፡ ይህ ፈጣን የቴክኖሎጂ ዘመን ግን የነጠቀንም ሀብቶች ትንሽ አይደለም፡፡ ባህላችንን፣ እና የመኖር ዋስትናችን ለዋቢነት በቂ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡

ወላጆቻችን ሃይኖታችውን ይዘው ርጋታ በሞላበት ኑሮ ዘመኑ በፈቃደው ሁኔታ መና ብሎው ኖረዋል፡፡ እኛ ደግሞ ከቴክኖሎጂ ወጣቶች ሁካታ ጋር ርካታም ሳናጋኝ እንደተነጫነጭን እንዳለን አለን፡፡ ጊዜው ከመጠቀም አኳያ ወላጆቻችንም እኛም ዛሬን እንደሰት በሚለው ዘይቤያቸን ጊዜውን ቁም ነገር ሳንሰራበት አያሳርፍ ነው፡፡

ምናልባት እኛ ከተዘናጋንበት ለመንቃት አሁንም ጊዜ አለን፡፡ ነገር ግን የተበታተነውን ትኩረታችንን አሰባስበን በመወያየት አንድ ነገር መጀመር አለብን፡፡ ወቅቱ እያለፈብን ከሄደ ለልጆቻችን የምናወርሰው ጉዳት ልጆቻችንን ወደፊት የሚያሳርፍ እንዳይን ጥረቱ ከዛሬው ይጠበቅብናል፡፡

ልጆቻችን የሚኖሩበትን አካባቢ አለፍ ብለውም ሀገራቸውንላቅ ሲልም ዓለማችንን በጊዜው እንዲውቁና ለማህበራዊ ኑሮ ጥሩ እውቀት እንዲኖራቸው በቤትም ሆነ በት/ቤትም የቀን ተቀን ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡

ከሀገራችን ጥያቃዊነት አኳያ ዘሬ ያለንበት ሁኔታ በተለያየ መድረከ ሲገመገም ብዙም ፈቅ አለማለቱ ለምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ከህሊና ወጥቶ በአደባባይ የታረክ ሊቃውንት፣ የስነ-ልቡና ጠበብቶች፣ ሌሎችም የማህበራዊ ሳይንስ ጠበብቶች ሊነጋገሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጭንቅላት እየተገገዋለለም ዐማታት መቁረ አሁንም የቀጣይን ትውልድ ዓይን ሽፍኖ ራስንችለህ ሄድ ከማለት አይለይም፡፡

አያቶቻችነ ኖረው አልፈዋል፡፡ ወላጆቻችንም ሲሰሩ የሚችሉበትን ጊዜ ጨርሰውታል፡፡ ነገር ግን ለልቻቸው የሚነገሩትና ለለንበት ደረጃ ምክንያት የሚሆን አያሌ አውነታዎችን ለመሰክሩልን ይችላሉና የቀራቸውን ጌዜ ከመጠቀም ባንቀጥብ ብልህነት ይመስለኛል፡፡ እኛም የተወሰነ መሰሪያ ጊዜ አለን፡፡ /የት ለመድረሰ ካልተባልኩ፡፡/ ለልጆቻችን ዋና ቀናውን ካሁን ማውረስ መቻል ተገቢነው ባይነኝ ገን ህይወት ምንድን ናት?

7


ህይወት? ክፍል 7
በእርዳታ እየተደገሙ ከረሃብ ድነዋል፡፡ ለድርቅ መስፋት የአዞን መቀድድ ድርሻ ያኑረው እንጂ ከቦታ ምክንያቶ ይለያያሉ፡፡ የተባይ፣ የአረም በሽታዎችም ከመከላከል አቅም በላይ በሆኑበት ቦታ ትንሽ የማይባል ጉዳት አድርሰዋል፡፡

በመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጎርፍ ለመጥለቅለቅ፣ እሳት ቃጠሎ በመሳሰሉት ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮ ህይታቸው ያለፈው፣ የአካል
… አይ ጊዜ አይ ጊዜ… ብዮ ብጀምር ግዜን መወንጀል እንዳይመስልብኝ ፈራሁ በእርግ የልማት ክንውኖችም ሆኖ የጥፋት ድርጊቶች በጊዜ ውስጥ ያልፈው፡፡ ለልማቱ አስየው ሲባልለት ለጥፋት እርግማን አይቀርለትም፡፡

በዘመናችን ብዙ ጥሩ ነገሮች እንደታዩና እንደተከወኑ ሁለ መአቶችም ተከስተዋል፡፡ ለምሳሌም ያህል የአካባቢው አይር መሳሳትና መቀደድ በውጤቶም ኋይለኛውን የፀሐይ ጨረር ንዳድ በምድር እንዳንድ ቦታዎች ላይ የአየር መዛባትን እስከትሏል፡፡ የእርሻ መሬቶች ደርቀዋል፡፡ ብዙዎችም ጉዳት የደረሰባቸው፣ የእድሜያቸውን ያካበቱት ንብረታቸው የወደመባቸው፣ ቤተሰባቸው ተበትኖቻቸው የተሳቀቁ እጅት ብዙ ናቸው፡፡

አሳሳቢውና የሰው ልጆች አፈጣኝ መፍትሄ ሊያደርጉለት የሚባው ደግሞ ሰው ሰራሽ የአካባቢ ግጭቶችን በውይይት እንዲፈቀ ማድረግ ነው፡፡ በምስራቅ አፍር ጎረቤታችን በሆነቸው ሶማሊያ በመካሄድ ላይ ያለው የፖለቲካ ብጥብ ሀገሪቱን በሰው ህይውትና በኢኮኖሚ እያዳሸቃት ነው፡፡ ህዝቦቿም ወደ ጎረቤት ሀገሮች ስደት ተዳርገዋል በአንጉላ፣በደቡብ አፍረካና በዩዝላቪያ የተፋፋመ የእርስ በርስ እልቂ ችል ተብሎ ሊታይ አይገባውም፡፡ በእርግጥ አሁን በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የፖለቲካ ፓርቲዎች ለነፃ ምርጫ ፉክክር ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም፡፡ ነገር ገን ከረጅም ዓመታት በፊት የተጫረውን እሳፈት ማጥፋት አለበት፡፡

የሰው ልጅ የኑሮ አቋም በበሽታውም ወገን በጣም አስከፊ ዕጣ ድርሶታል፡፡ ኤድስ፡፡ በሽታ ከተፈጥሮ ጋር የተቆራኝ መሆኑ ቢታወቅም የመስፋፋቱ ጉዳይ ግን ሰው ሰራሽ ነው ማለት የሚቻልበት ደረጃ ተደርሷል፡፡ ምክንያቱም የበሽታ መዛመቻ መንገዶችን በጸመለከጸ መግናኝ ብዙኃን ከመቼው ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ተምህርታዌ መግለጫዎን፣ ማስታወቂያዎችን አሰራጭተዋል፡፡ በተለያዩ የበጎ አላማ ማህበራት በራሪ ወረቀቶችን … የህይወት ጃኬቶችን … እከፋፈለዋል፡፡ ነገር ገን አልፎ የሚነገረው የበሽተኞች ቁጥር መጠን ከፍ ለማት ግን የሰው ልጆች ለሚሰጡት ትምህርቶቸ ልቦናቸውን እንዳልሰጡ ያመለክታል፡፡

በአንድ ወቅት ከወደ ሩቅ ምስራቅ የተደመጠው ዜናም የሚዘገንን ነው፡፡ በህንድና በታይላንድ የኅህጻናት ሽያጭ፡፡ በለጋ ዕድሜያቸው ወደ ሽርሙጥና ዓለም የሚደረጉት ህጻናት ዓይናችውን ከፍቅረተንዋይ ያሳወራቸው አረመኔዎ ነው፡፡ ይህ በዚህ እንዳይቀጥልም መላው የሰው ልጅ በአጭሩ ለመቅጨት መፍትሔውን መሻት ያስፍልገዋል፡፡

ከኢጣሊያ ያለው የማፊያ ድርጅትም ለህግ ወጥ ድርጅቱ መበልጸግና የማሕበረሰቡን ሰላም ሰቆቃ እንዲመላበት ድርጅቱን አጥብቀው የሚቃወሙትን የፐሊስ ኃይሎች፣ የፍርድ ቤት ዳኞንና የመንግስትን ባለሥልናት በየቦው ከነቤትሰቦቻቸው እየፈጁና የህዝቡንም ሰላማዊ ኑሮ አያደፈረሱ ይገኛ፡፡ የኩልምቢያ የአደንዛዥ ዕፅ ተደጃሮች ከኢጣሊው ማፊያ ከሚያደርሰው በደል አይደለም እየፈፀሙ ያሉት፡፡

ባሁን ጊዜ ስላሎች ችግሮች ሙሉ በሙሉ መጥቀስ አባይን በጥፋት ይሆናል፡፡ ለነገሩ ግን ህይወት ምንድን ናት?

6


ህይወት? ክፍል 6
በሃገራችን የእግር ኳስ ስፖርት ሲነሳ አብረው የሚነሱ ስፖርተኛ ከጅምሩ አሁን እስካለበት ድረስ ያደረሱ፣ ከሃገርም አልፈው በአህጉና በዓለም በከፍተኛ ደረጃ የታወቁና ከብር የተለረሳቸው ድንቅ ክቡር አቶ ይድቃቸው ተሰማ ይጠቀሳሉሉ፡ የአንጋፋው የስፖርት ሰው በአካል ባናገኛቸውም የህይወት እያሉ የፈጸሟቸውና እየጉላ ነው፡፡ …ስፖርትና ጎጂ ባህሎች ሌጣመሩ አይገባም ስለዚህም በስተዲየሞች ያሉ የጎጂ ሱስ ማስታወቂያዎች መነሳት አለባቸው፡፡ … አፍሪካን በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ዋንጫ የሚወከሉ ቡድኖች ቁጥራቸው ከፍ ማለት አለበት… የሚሉት ነጥቦችን ማቅረብ ለቅሱስ ዓላማቸው ቁርጠኛነታቸውን ሲያሳዩ የሚችሉ ምሳሌዎች ናቸው፡፡

እንዲያውም ቅዱስ መጽሐፍ ላይ … ነብይ በእግሩ አይከበርም… እንዲሉ ካልነ በቀር ለክቡር አቶ ይድነቃቸው መታሰቢያ እስካሁን እንድም አለ መደረጉ ወይም ሲመከር አለመስቱ ወይ ጊዜ፣ ወይ ጊዜ እያሰኝ የስፖርት ቤተሰቦችን ማንገብገቡ በብዙ ቦታ ይደመጣል፡፡ በዓለም ደረጃ ብዙ የተነገረላቸው እኚህ … የጀብራልተሩ አለት… ሞሮኮ ውስጥ አንዱ ስቴዲየም በስማቸው መሰየሙ ለኛ ፌዴሬሽን ጆሮ አልደረሰ ይሆን?

ከእግር ኳስ ስፖርት ሳንወጣ የጊዮርጊን ሺ መለያ ቁጥር 8/ን/ ለብሶ የጎል አካባቢውን ሜዳ /ቃላቶቻችን እንደሚያስታውሱት/ በቁጥጥሩ ሥር የሚያደርገው የጎል ካፒታኑ መንግስት ወርቁ ጨዋታም ካቋረጠ በኋላ በአሰልጣኝነት ገፍቶበት ከአፍሪቃ አሠልጣኞች ቀዳሚነቱን ደረጃ የያዘ በሙያው አንቱ የተባለ ሆኖ በተወለደበት ሀገር ላይ ግን ለ ጡረታ መሰናበት አያደር መገረሙ አይቀርም፡፡

ያደላቸው ቸሎታ ያለውን ከሌላ ሀገርም ቢሆን ለምነው፣ ተደራድረውና ተንከባክበው ያስሩታል፡፡ ከእኛው ሀገር ግን የሀገሪቱን ብርቅ ልጆች የሚያቆሉ ሁኔታዎ ገጥመውናል፡፡ አረ ወገን ዜው ካለፈ በዋዛ የሚተኩ ሰዎች አይደሉምና ተገቢውን ትኩረት እንንፈጋችው፡፡

ስለክቡር አቶ ይድነቃቸው የአለም ጋዜጠኞች የመሰከሩላቸው ራሱ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው፡፡ …ከመቀረት መዘግየት… ይሻላልና እንተባበር፡፡

ከሀገር ወጣ ብለን ደግሞ እሰኪ ወደ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ አሬና ላይ ባለፉት ቅርብ ዓመታት ሲወደስና አብረውት ከሚጫወቁት ግዝፎ የወጣውን ማራዶናን ለአፍታ እናስበው፡፡

ይህ የአረጀንቴናው ተወላጅ ዲዮጎ ማራዶና በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ የሀገሩ ስም ሁለት ጊዜ ያስጠራ የሀገሪቱ ብርቅ ልጅ ነው፡፡ በጨዋታው ድንበር ተሸግሮና ውቅያኖስን አቋርቶ ጣልያን ክለቦች ረዘም ላለ ጊዜ ሲጫወት በዓለም ላይ ስ ከዳር እስከዳር ናኝቷል፡፡ ሀብፈትም ጉርፎለታል፡፡ በስፖርት ዕቃዎችና የተለያዩ ነገሮች ላይ ስሙን ማስተዋወቁም አድርጎ ተዝቆ የማያልቅ አግኝቶበታል፡፡ ለማራዶና ኑሮ ግን ብዙም አልተመቸውም፡፡ በፍቅሩ ወይንም በግንዘቡ የተጠመዱ ሴቶች አላስወጣ አላስገባ እያሉትና ሁለቱ ያህልም ይወስዳል በሚል ክስ ፍዳ መክራውን አይቷል፡፡ የማፊያ ቡድንም ዋ አያለው ቆይቷል፡፡ በእግር ኳስ ከፍተኛ ዝነኛ ሀብት ያገኛው ማራዶና ስሙ በቤትና በሃሺሽ ተበጠልጥሏ፡፡ ኑሮ የሚባለው አባዜ ትንሹንም ትልቁንም በትለያዩ ሁኔታዎች አያሠጋው ነው፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?

5


ህይወት ? ክፍል 5
በዓለም ላይ ስንኖር በፈለግነውና ባሰብነው መንገድ ሳይን እያንዳንዷ ቀን ባልተገመተው ሁኔታ ነው እየከነፈች ያለችው፡፡ ምክንያቱ ግን ለብዙዎቻችን ግልፅ አይደለም፡፡ በርግጥ በግላችን ኑሮም ሙሉ በሙሉ ወሰኝ አኛው ባለመሆናቸን ለነገሩ አስተዋጾኦ ይኖረዋል፡፡

ከእኛነታችን ስንነሳ በጤንነትና በማህበረሰቡም ተቀባይነት ኖሮን ለመቆየት የተወሰኑ ያልተጻፋ ህጎችን መጠበቅ ይኖብናል፡፡ ለምሳሌም ብንወስድ የግል ጽዳታችንን የቀን ተቀን ክትትል አድርገን መጠበቅ የሃይዲን ሳይንስ ህጉን በተለይዩ ሁኔታዎ አቀበሉናል፡፡ ይህን ህግ ካልጠበቅን ጥገኛ ነፍሳት ሰውን መቅረብ እስኪያሳፍሩን ድረስ ሊጎዳኙን ነው፡፡ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብም ካልተመገብን የውስጥ ተሃዋስያን ሆዳችን ውስጥ እየጯጯሁ ጤናችንን ሲያናጉትና ከማህበራዊ ህይወት ሊያርቁን ይዘጋጃሉ፡፡

በቤተሰብ የኑሮ ተቋም በእኛነታችን ለቤተሰቡ ፍቀር ስንል የምንከፍላቸው ግዴታዎች ወይም ያልተጻፉ ህጎች ያስጠነቅቁናል፡፡ ከነኝህ ግዴታዎች አንዱ ካልተሟላ ያለን መዋደድና መተሳሰብ አደጋ ላይ መሆኑንም ለማወቅ … ኮሌጅ መበሠስ የሚያሰፈልገው … ጉዳይ አይንም፡፡ እያንዳንዱ አባል የቤተሰብ ፍቅር ፀንቶ መኖር ከፈለገ ከሱ የሚጠበቀውን ግዴታ መወጣት አለበት፡፡

ቤተሰብ ያለ ጎረቤትም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ይፍጥራል፡፡ መኖሪያችን በአጥር ስለተከለለም አትድረሱብኝ የማለት ደረጃ ከባህልና ኤኮኖሚ አቋም እንኳን ስንገመገም አልደረሰንም፡፡ ስለዚህም ቤትና ጎረቤት ዘንከን ሳይግጥማቸው ኑሮን ለመግፋት አሁንም በውስጥ የሚታወቁ ድንጋጌዎ ይኖራሉ፡፡ ጎረቤት ልብስ አያጠቡና አያሰው ከሆነ ቤቶቻችን ጣላቢ ቆሻሻ ለማቃጠል መነሳት የለባቸውም አለያ በዘልማድ የታወቁት ድንጋጌዎች ጥሰው ከጎቤት ይቀያየማሉ፡፡ ከቤት ግብዣ ኖሮ ተጋዛዥ በሙዚቃ መደሰት ካለበት የጎረቤትን የእረፍት ቀን ወይንም የእንቅልፍ ሠዓት ማደፍረስ አይገባም፡፡ ድንጋጌዎች ከተበላሹ ገን የከፋ ቀን ደራሽ የጎረቤት ወዳጆችንን ልቤ እንዲርቀን ምክንያት ሆነዋል፡፡
እንግዲህ ጎረቤት ካስቀየምን ስማችንም ማህበረሰቡ ውስጥ ሲነሳ ነው፡፡ ማህበረሰብ የሰፋ ደረጃ ቢኖረውም በዕቁቡ፣ በዕድሩና ሌላም የመረዳጃ ማህበራት ውስጥ ለመቀጠል ያልተጻፉትንም ሆነ የተፃፍጽን ህግጋት ማክበር ቀዳሚ ግዴታችን ነው፡፡ ከማህበረሰብ መውጣት ማለት ከባህር ውስጥ የወጣን አሣ መሆን ነውና፡፡

ከዚህ ላይ ያልተፃፉት ህጎች ሙሉ በሙሉና ከተጻፍትም በከፊል ሰው በማህበረሰቡ አዛውንቶች ይመከራል፣ ይወቀሳል፣ ይቀጣል፡፡

አንድ ሰው በሌብነት ወንጀል ቤከሰስ ህግ ተላልፏልና በፖሊስ ታድኖ ፍርድ ፊት ይቀርባል፡፡ እዚህ ላይ እንግዲህ እንደ ህግ አስከባሪ ሆኖ ፖሊስ ተጨምሯል፡፡ ሥራውም አጥፊዎን እያደነ ለጥፋታቸው ፍርድ እንዲቀበሉ ማድረግ ስለሆነ ተገቢ ቦታ አለው፡፡ የፖሊስ የስራ ተግባሩ ለማህበረሰቡ በጣም የተቀደሰው ሲሆን በዚህ ሙያ የሚሰማራው ሰው ራሱ ህግ ተላላፊ ወንጀላኛ ለሆነስ? የህግ የበላይነት አበቃ ያስኛል፡፡

ስላልተጻፈም ሆነ ስለተጻፈ ኅግ ከሁሉም በፊት የህሊና ፍርድ ወይም የህሊና ሚዛን ወሳኝነቱን ለሰዎች ልጆች ባይደበቅም የህሊና ሚዛኑ በብዙዎች ዘንድ ከተረሳ መቆየቱ እህህ …… ያስብላል፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?

4



ህይወት? ክፍል 4
በመዲናችን አውራ መንገዶች መተላለፊያ ላይ የትራፊክ ህግ እስኪፈቀድላቸው ቆሞ ከሚሎ እግረኞች ወይንም ባለመኪኖች … የዳቦ መግዣ ሣንቲም … እርጥባን የሚለምኑ አንድ ፍሬ ልጆች መታየት ከጀመሩ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው፡፡ ልብሳቸው እላያቸው ላይ ያለቀ፣ ሰውነታቸውን ውሃ ከነካው የሰነበተ፣ የቀኑ የፀሐይ ሐሩር፣ የማታው ብርድና የጠዋቁ ውርጭ ገላቸውን ያደነዘዘው እነኝህ አምቡ ልጆች ገና በዚህ ትንሽ ዕድሜ ለዚህ ሁሉ ፍዳ መዳረጋች ለምን እንደሆነ ለሚጠይቁበት ሩቅ አይሆንም፡፡ ከልመናቸው ባሻገር እርጣባን የሚወረውሩላቸወን ሰዎች፣ ፊት ነሰተው የሚያመናጭቋቸውን አለፍ ሲልም የሚሰድቧቸውን በልጅ ጭንቅላታቸው ቀርፀው የሚይዙት ምናልባትም ከሜችሉት በላይ ይሆናል፡፡

እዛው የመኪና መንገዶች ላይ ከመንገድ ወጣ ባለች አነስተኛ ቦታ ትናንሽ ጎሎች ሠርተው በጨርቅ ኳስ ቀልባቸውን አጥተው የሚጫወቱ ደግሞ እሱ ለዛውም በባዶ እግራቸው፡፡ ጎሎች አካባቢ የት/ቤት ደብተሮች አልፎ አልፎ አይጠራም፡፡ እነኝህ አንድም ከት/ቤት ቀርተው አለበለዚያም የት/ቤት የወር ክፍያ በወቅቁ መክፈል ሳይችሉ የተባረሩ ናቸው፡፡ ወላጆቸው የወር ክፍያውን ከእጅ ወደ አፍ ከሆነች ኑሯቸው ቀናንሰው እስኪከፍሉ ድረስ በመንገድ ዳር ኳስ ጨዋታ ነፍሳቸውን ያስደሰታሉ፡፡ የወር ክፍያ ሳያቋርጡ እየከፈሱና ደህና እየለበሱ በሜማሩት ጓከኞቻቸው በትንሿ ልባቸው እየቀኑ፡፡

ከእነሱ በዕድሜ ብዙም ያልራቁ በቤተሰብ ተጽዕኖ ከትምህርት ሠዓት ውጪ ሊስትሮ፣ ጋዜጦች፣ ሎተሪ እና ሌላም ሸቀጦች ይዞው በአንድ በኩል ቤተሰብ እየደገሙም የሚኖሩ ልጆች ብዙ ናቸው እነዚህ ልጆች ከእንዳንዶች በቀር ት/ቤት የተሰጣቸውን የቤት ሥራዎች በአግባቡ እየሰሩና እያጠኑ ከክፍል ወደ ክፍል የሚሸጋገሩት በጣም ጥቂት ቢሆኑ ነው፡፡

ከዚህ ዕድሜያቸው ትምህርትም ሥራም አቅማቸው የሚፈቅደው አይደለም፡፡ ከትምህርት ሠዓት ውጪ ካልሰሩ ደረቅ ዳቦ እንኳን ሲያረባቸው ነው፡፡ የቤተሰባቸው የኑሮ አቅም ደግሞ አያወላዳም፡፡ ያላቸው ምርጫ እንደምንም ተሯሩጠው መኖር ነው፡፡ የልጅነት ጨዋታ በልጅነት ዕድሜ አያምራቸውም ገና በልጅነታቸው ችግር ብዙ አስተምሯቸዋል፡፡

በታዳጊ ዕድሜ ያለ ሌሎች ደግሞ አሉ ከቤት ወደ ት/ቤት ከት/ቤት ወደ ቤት ቤት እንደደረሱ እረፈት አድርገው፣ የቤት ልብሰ ይቀይራሉ፡፡ መክሰስ አማርጠው ይቀርብላቸውና ከግቢ ሳይወጡ ይጫወታሉ ከጨዋታ በኋላ ወደ ጥናት፡፡ በማግስቱ ቆንጆ የት/ቤት ልብስ ከዘመኑ የልጆ ፋሽን ልብሶቻቸው ለዚያ ቀን ደስ ያላቸውን ለብሰው በሜወዱት የምሳ ዕቃ ምሳቸውን ይዘው ወደ ት/ቤት፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ያለይዋቸው የቪዲዮ ካሴቶች ይመጡላቸዋል፡፡ ከት/ቤት ጓደኞቻቸው ጋር ስልክ ይደዋወላሉ፡፡ የሚሂድባት የቤትሰብ መኪና የትራፊክ መብራት ሲያስቆማት አኒያ የመንገድ ላይ እርጥባን ፈላጊ አንድ ፍሬ ልጆች ወደ መኪና መስተዋት ጣጋ ብለው እጃቸውን ይዘረጋሉ፡፡ መኪና ውስጥ ያሉት የቤት ልጆች አይስክሬም እየላሱ ሲሳሳቁ ለእርጥባን የቆሙት አንድ ፍሬ ልጆች ያዩዋቸዋል፡፡ … አቤት ባርኔጣ እቤት ቀሚስ ደግሞ የሚባሉት ነገር ሲያስጎመጅ … ምራቃቸውን ሲወጡ አባትና እናት የመኪና መስተዋቶችን ግጥም አርገው ዘግተው በዚህ … ደባሪ … የትራፊክ ቀይ መብራት ላይ ኮተር ብለው ያፈጣሉ፡፡ ለእርጣባን የተዘረጉት እጆች መኪናውን መዳበስ ሲጅምሩ ቀዩ መብራት ጠፈፍቶ ቢጫና አረንጓዴ ሲበራ በደመ ነፍስ ወደ መንገድ ዳር ወጣ ይላሉ፡፡ መኪናዋም እኒን ቆንጆ የለበሱ ህጻናትን ይዛ ትፈተለካለች፡፡ እርጣባን ፈላጊዎቹም ዓይናቸው እንደተንከራተተ፣ ዕንባ እንዳቀረረ ሌሎች ተረኛ መኪኖ ይጠብቃሉ፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?