Friday, June 12, 2009

1


ህይወት ? ክፍል 1
… ማን ነበረ ይች ዓለም የተውኔት መድረክ ናት ህዝቦቿ ናቸው … ያለው? እኔ ሌላ መስፈሪያ ፍለጋ አይደለም ዓላማዬ በዚች የተውኔት መድረክ ተዋናዮቿን እላይ እታች፣ አንዴ ሐዘን ሌላ ጊዜ ደስታ፣ እንዲያፍሩ ደግሞ እንዲጠሎ፣ እንዲፈሩ እና እንዲደፈሩ፣ እንዲራቡ አለያም እንዲጠግቡ ወዘተ … የሚያደርጋቸው የተውኔቱ ድርሰት ልበለው? ህይወት ላይ ነው ትኩረቴ፡፡

አንድ የስራ ባልደራባዬን ነበር ህይወት ምንድን ናት ብዬ የቡና ዕረፍታችን ላይ የጠየቀቀኋት፡፡ … ሁሉም ነገር /ድርጊት/ ህይወት ነው በማለት ከጀመረችልኝ በኋላ ህይወት የተቃራኒ ገጠመኞችና ክስተቶች ጥርቅም ናት፡፡ … አለችኝ፡፡ እኔም ከሷ አባባል ተነስቼና ከፈላስፋው ጥያቄ ጋር በማቆራኝት የትኩረቴ መንደርደሪያ አደረግሁት፡፡

የህይወት የትናንሽ እስረኞች ጥርቅም ናት፡፡ /በግርድና ትርጉመ/ የሚል መንፈስ ያለው የእንግሊዝኛ ጥቅስ ከረዥም አመታት በፊት ማስታወሻ ደብተሬ ላይ ማስፈሬ ትዝ ይለኛል፡፡ ይህንን ጥቅስ ያፈለቀው ሰው በህይወት ትላልቅ ነገሮች የሜሌቸው ነገሮች ያልተጠመው በሌሎችም ህይወት እንዲሁ በሱ ግምት ትናንሽ ነገሮች ብቻ ሲከውኑ የመስከረ ይመስለኛል፡፡ /… ይመስለኛል የሚለው ቃል ሞኞች የፈጠሩት ቋንቋ ነው … ባትሉኝ፡፡/

ይህን አባባል በአንድ ወቅት የተገናሩት ሰው /አሁን ነፍሳቸወን ይማረውና/ ህይወታቸውን የኖሩት በሥራ ተጠምደውና መጻህፍትን ሲያነቡ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አንድ ጊዜ በክፍላቸው ያለ ሰራተኛ ለነገ ፈቃድ ይስጡኝ ወንድሜ ያገባል ስለዚህ ለሰርጉ አንዳንድ ሥራዎን ማገዝ አለብኝ ይላቸዋል፡፡

ሰውየውም ዕድሜ ርጋታን ባለበሰው ድምጻቸው … ነገ ሥራ አለ፡፡ ይልቅ ወንድምህን ሌላ ቀን እንዲያገባ ንገረው፡፡ … ብለውት በእጃቸው ወደያዙት ወረቀት አቀረቀሩ፡፡ … በማለት ያጫወተኝ ፈቃድ ጠያቂው ሠራተኛ ነበር፡፡ እኝህን ሰው አጋጣሚውን አገንቼ ህይወት ምንድን ናት? ብዬ ብጠይቃቸው ኖሮ … ህይወት ሥራ ናት … አይሉኝም ትላላችሁ?

አንድን ሰው በሃሳባቸው ባሉት መካከለኛ ቀመት፣ ነጻት አቆላላፍ የተዛነፈና ጽዳቱም ያልተጠበቀ፣ ድፍርስ አይኖችና የረሳውን ዕቃ የሚያሳለስል ዓይነት መፍዘዝ የሚታይበትን ሰው … ህይወት ምንድን ናት? … ብትሉትና ከመቅጽበት … ጠጅ … ባላችሁ ትገረሙ ይሆን? እኔ አይገርኝም ምክንያቱም ይህን የጠጅ ወዳጅ ጠጅ በማይጠጣበት ጊዜ ህይወት አስፈሪ አቦ ሃማ ዓለም ትሆንበትና ለሷ እሾና አስፈሪነት ለመሸሸግ የጠጅ ጋሻ አስፈላጊው ነውና፡፡ /እኔ ግን ጠጅ ሲሸተኝ አልወድም፡፡/

ቦሌ አካባቢ ያለውን የህይወት ተውኔት ተመልክታችሁ ወደ እኛ ሰፈር ደግሞ ብቅ ብሎ፡፡ ልዩነት የተ የለሌ ነው፡፡ መምባሳም ህይወት አለ ሞቃዲሾም እንዲሁ፡፡ ሄሮሺማና ናጋሳኪም ይኖራል፡፡ የህዋይ ደሴቶችና ቤቨርሌሄልስም እንዲሁ፡፡ ሁሉም ቦታ ህይወት አለ የሰማይ ምድርን ያህል ርቀት ያህል፡፡ /ግን የሰማይርቱ ከመሬት ምን ያህል ይሆናል?/ ተዉት ተዉት የመጀመሪያውን ጥያቄ መልሱ፡፡

አንድ የሳንንስ ፕሮፌሰር ጋዜጠኛው ለጠየቃቸው መልስ ሲሰጡት እንግዲ አስቸጋሪ ጥያቄ ስትጠይቃቸው ህይወት ምንድን ናት ብለው ብተጠይቁኝ ይሻል ነበር ብለው ይመልሳሉ፡፡ … በማለተት ስለጥያቄው አስቸጋሪነት በብልሃት እንደመለሱለት አንድ ከወደ አወሮፓ በኩል የዘለቀ የወጣቶች መጽሔት ላይ እንብቤያለሁ፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?

…../

No comments:

Post a Comment