..የሰው ነገር !
ዮናስ ቁመቱ ዘለግ ያለና ሰውነቱም ሞላ ብሎ ፊቱ ብዙም የማፈታ ወጣት ነው፡፡ በአንድ የመንግስት መስፈሪያ ቤት ከተቀጠረ ሁለተኛ አመቱን ይዛል ፡፡
ለሥራው ብዙ ትኩረት ቢያደርግም ዛሬ ግን ቀኑ ካፊያ ሆኖ ስለዋለ እሱም ደብሮታል ፡፡ የሚሰራበት ክፍል የሂሳብ ክፍል እንደመሆኑ ከሱ ጋር 5 የሚሆኑ የሥራ ባልደረቦች አብረውት አሉ፡፡
ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ሁሉንም በአይኑ እንደመቃኘት ብሎ ተንጣለለ፡፡
.. ቶምቦላ ልግዛና ልምጣ እስቲ .. ብሎ ከወንበሩ ሲነሳ እንደኛዋ ያሥራ ባልደረባው ቀና ብላ .. ዮኒ እስቲ እባክህ ለኔም ግዛልኝ ..ብላ ከቦርሳዋ 5.00 ብር አውጥታ ትሰጠዋለች ፡፡
ተቀብላት ይወጣል ፡፡
የመስሪያ ቤቱ በረንዳ ጋር ሲደርስ ካፊያውን እያስተዋለ ቆመ ትንሽ ከራሱ ጋር እንደመሚገት ብሎ..በዚህ ካፊያ ምን አስወጣኝ .. በሚል ሀሳብ ወደ ሚሰራበት ክፍል ይመለሳል፡፡ ሎተሪ ለሳም እንዲገዛላት ለሰጠችው ልጅ ዝርዝር አጣሁ ብሎ ገንዘቧን ይመልስላታል የቀኑ ስራ ሰዓት ማለቁ ስለሆነ ወደ የቤታቸው ለመሄድ ጠረጴዘዋቻቸውን አዘገጃጁና ተበታተኑ፡፡
በማግስቱ ጠዋት የተለመደ ስራቸውን በመስራት ላይ እንዳሉ ከቅርንጫፍ መስሪያ ቤት የመጣች ልጅ ..ዮናስ ይሀውልህ እኛ ጋር የሚሰሩ አንድ ሽማግሌ ቶሞቦላ ገዝተው በአንድ ቁጥር ስህተት 30.000 ብር አመለጣቸው ይህውልህ ሎተሪው.. ብላ ትሰጣዋለች፡፡ ዮናስም ቀበል አድርጎ .. የትኛው ቁጥር ነው ይላታል ይቺ ሶስት ቁጥር ስድስት ብትሆን 30.000 ብር አፍሰው ነበር.. ተለዋለች፡፡
ዮናስ ይህን ጊዜ ትንሽ ሳቅ ይለው ጀመር፡፡ ›› ለመሆኑ አንቺሥ ቶምቦላ አልገዛሽም ነበር .. .. አረ ገዝቻለሁ ይሀውልሀወ ቁጥሩ ግን ምንና ምን ተገናኝቶ ፡፡..
ይህን ጊዜ ከሳ የተምቦላ ሎተሪ ላይ ስድስት ቁጥርን በምላጭ ቀስ ብሎ እውጥቶ አንድ ቁጥር ብቻ የተሳሳተበት ሎተሪ ላይ በብልሀት ይለጥፉታል ፡፡ በደንብ ከደረቀች በኃላ አጥፎ ኪሱ የጨምራታል፡፡
የሻይ ሰዓት ሲደርስ አንዲት ሠራተኛ መጥታ እስቲ ቶምቦላ የገዛችሁ ማታ ከቴሌቪዝን ላይ የአሸናፊ ቁጥሮች ዝርዝር ጽፋያለሁና ልይላችሁ ፡፡
ሎተሪ የገዙ በሙሉ እያወጡ ይሰጡት ጀመር ሁሉንም እያየች የላችሁም እያለች ትመልሳለች ወደ ዮናስ ዞር ብላም ..ዮናስ አንተ አልገዛህም እንዴ እስቲ ልይልህ ..ትለዋለች ዮናስም እንደ ዘበት ኪሱ ገባ ብሎ ያንን እስተካክሎ የለጠፈውን ሎተሪ ይሰጣትና ጨዋታውን ከአንድ ሰው ጋር ይቀጥላል ፡፡
እሳም ሎተሪውን እያስተያየች ደንገጥ ትልና ..ዮናስ 30.000 ብር ደርሶሀል..ብላ ትጮሃለች ፡፡
ዮናስም ቀና ብሎ ያያትና ..አባክሽ አትቀልጅ ! ብላት ፊቱን አኮሳትሮ ጨዋታውን ይቀጥላል ፡፡ .. አረ አባቴ ይሙት ገብርኤልን /.. ትለዋለች ያልሰማ መስሎ ጨዋታውን ይቀጥላል ፡፡
በዚህ ጊዜ ሌሎችም ከመቀመጫቸው ብድግ ብድግ እያሉእሳ የምታስተያይበትን ወረቀትና ሎተሪ እየተቀባበሉ ያዩትና እውነት ነው እያሉ ይጫጫሁ ገቡ ፡፡
ዮናስም ወደ እነሱ ዞር ብሎ ..አንቺ ጽፈሽ ጨምረሽበት የሆናል የኔን ሎተሪ ቁጥር ..ይልና ይኮሳተራል ፡፡ ልጅታም ..አረ ዮናስ አባቴ ይሙት ስል በውሸት ሰምተህ ታውቃለህ ..ብላ ድምጻን ታለሰልሳለች፡፡
በዚህ ጊዜ ከተሰበሰቡት መሃል አንደናዋ ..እኔ ስልክ ደውዬ ላረጋግጥ .. ብላ ወደ ብሄራዊ ሎተሪ ስልክ ትመታለች ፡፡ ተቀባይ ስታገኝ ..የኔ እመቤት እባክዋን ትላንትና ማታ የወጣውን ቶምቦላ አሸናፊ ቁጥሮች ማወቅ ፈልጌ ነው ሊነግረኝ ከቻሉ ..ትላለች፡፡ ከብሄራዊ ሎተሪ ስልኩን የተቀበለችውም ዝርዝር ንባቡን ከጀመረች በኃላ ታቃርጥና ..የኔ እመቤት የእርስዋን የቶምቦላ ቁጠር ቢነግሩኝ ጊዜን እንቆጥባለን ትላታላች ፡፡ በዚህ ጊዜ ልጅታ በእጃ ላይ ያለውን የሎተሪ ቁጥር ታነባለች በብሄራዊ ሎተሪ በኩል ትንሽ ዝምታ ይሰፍንና ረጋባለ ድምጽ ..የኔ እመቤት እንካን ደስ ያለዎት የ 30.000 ብር ባለዕጣ ሆነዋል..ትላታለች፡፡ ልጅታም ትንሽ ተርበትብታ .. አመሰግናለሁ .. ካለች በኃላ እጇን እንደ አሞራ ክንፍ ዘርግታ ..ልክ ነው !ልክ ነው ! 30.000 ብር 30.000ብር እያለች ወደ ዮናስ ሄደች ፡፡ አጠገቡ ስትደርስ ዮናስ ብድግ ብሎ ዓይናን ሲያያት የደስታ ዕንባ ዘለላዋች ሲንጠባጠቡ ተመለከተ እሱም ፈገግ ሎ ተቀበላት..እንኳን ደስ ያለህ ዮናስ ..አመሰግናለሁ..፡፡ በአካባቢው ያሉት ሠራተኞች አንድ ባንድ እየመጡ ..አንኳን ደስ ያለህ ዮናስ ይሉት ጀመር እሱም የኦሎምፒክ ማራቶን ሮጦ አሸንፎ ደክሞት ፈገግ እንደሚል ዓይነት ከተቀመጠበት እየተነሳ ..አመሰግናለሁ ..ሲለቸው ዓይኑን ከጥግ በኩል ከተቀመጠችው ትላንትና ለሳም ሎተሪ እንዲገዛላት ወደ ላከእው ልጅ ወርወር ያደርጋል ፡፡ እሳም በጊዜው ኦዲተር ስለመጣባት የሂሳብ መዝገብ እያስመረመረች አልፎ አልፎ በረዝሙ እየተነፈሰች .. አይ የሰው ነገር ! ትላለች ደግማ ደግመ
..ዮናስ ! ..የሚል ጮክ ያለ ድምጽ ተሰማ ሁሉም ወደ ድምጹ አቅጣጫ ፊታቸውን መለሱ በመስሪያየ ቤቱ ለ በአስተያየቱ ከሌሎች የማይገጥሙ አቶ የኔነህ ነበር፡፡ በዝርጋዳ አረማመዱ በሁለት እርምጃ አጠገቡ ሲደርስ ዮናስም የድካም ፈገግታ አአሳይቶት ብድግ ሲል ..እንካን ደስ ያለህ ! ካለውና ካቀፈው በኃላ ..አንድ ሳንቶም ሳታነሳ ባንክ አስቀምጠው ኦኬ ..ብሎት መልስ ሳይጠብቅ በመጣበት አካሃን ተመልሶ ወጣ ፡፡
..ይሄ ዮናስ ምን ዓይነት ድንጋይ ..ትላለች አንዳ የሥራ ባልደረባው ሌላም ..እኔ ከድሮ ጀምሮ ነው የዮናስ ቀዝቃዛነት ይገርመኝ የነበረው አሁን ደሞ መላ ቅጡ ነገር ነው ፡፡ ሰው እስቲ 30.000 ብር ደርሶት ጥሩ ፈገግታ እንካን አይኖረውም ባይፈነድቅም እንካን በስማም እቴ!
.. እሱ እባክሽ ገና በልጅነቱ ዓለም የበቃው አይነት ይመስላል ፡፡ ግን የተፈጥሮ ነገር ነው እኔንስ የሚገርመኝ ስንት ዓይነት ሰው አለ ድጭም አላለበት እኮ !
ከሌላ ክፍል የምስራቹን ሰምቶ የመጣው ገብል .. አቶ የኔነህ እንዳሉት በማስመሰል አነጋገርና እክት አንድ ሳንቲም ሳታነሳ ባንክ ልታስቀምጠው ነው ወይንስ ሃሳቡን ሳይጨርስ መጀመሪያ ሎተሪውን ከቴሌቪዝን ላይ ከጻፈችው የአሸናፊዋች ዕጣ ቁጥር ከዝርዝርጋር ያስተያያችው ልጅ ድንጋጤው አፍዛት ቆይታ እባክህ ውይይት ገዝቶ ቢያስነግድ ነው የሚሻለው .. ትለዋለች፡፡ ሌላም ቀበል አድርጎ ይልቅ ቆንጆ የንግድ ቤት በሽርክና ቢከፍት የሻለዋል ስትል በሩ ገርበብ ብሎ የነበረው ይንካካና ሲከፈት የሂሳብ ክፍል ኃላፊው ይገባል፡፡
ዮናስ ፈገግ ብሎ ከመቀመጫው ይነሳል ፡፡ ይጨባበጣሉ ..ዮናስ አሁን እንደሰማሁ ነው የመጣሁት እንካን ደስ ያለህ ! ..ዮናስም በማይለወጥ የደከመ ፈገግታው ..አመሰግናለሁ ..ይለዋል፡፡
የምስራቹ በመስሪያ ቤቱ ተዳርሶ ኖሮ ሰው ተራ በተራ እየመጣ ..እንካን ደስ ያለህ ..ሲለው ..አመሰግናለሁ ፡፡ እያለ ይመልሳል ፡፡ አብዛኛው ሠራተኛ የዮናስ ሁኔታ ቢያስገርመውም አንዳንዱ እርስ በርሱ ዮናስን ገምግመው ጨርሰውታል ፡፡
በቅርብ የሚያውቀው ራቅ ካለው ..እንዴት ያለ የዋህ ልጅ መሰለህ እግዚአብሔር እንደው የራሱን ሰዋች መርጦ ነው የሚሰጠው ማለት እችላለሁ..፡፡ ይላል፡፡
ሌላው ደግሞ ..ለሱስ እንካን ሰጠው ጥሩ ሰው እንዲያው የሰው መጨረሻ አይደለም እንዴ ለሱስ ይገባዋል.. ይላል፡፡
ዮናስ በአካባቢው ያሉትን ያስተውላል ከትግ የተቀመጠችው ልጅ ግን ..አይ የሰው ነገር ! .. ትላለች አልፋ አልፋ ለራሳ የምታወራ ይመሰል ፡፡
የምሳ ሰዓት ደረሰና ምሳ ለመብላት ወደ መስሪያ ቤቱ ካፍቴሪያ ዮናስና አንድ ወንድ ባልደረባው ሲሄዱ ..ዮኒ ኮንግራ ! በኃላ አናግርሻለሁ አሁን ቸኩያለሁ ፡፡ ..ይለዋል ከርቀት ሰው ጠራና ሁልጊዜ ችኩል ጌትነት ፡፡ ዮኒ ፈገግ ብሎ በጭንቅላቱ መልስ ከሰሠጠው በኃላ ወደ ካፊቱሪያው ገብተው ቦታ ሲያማርጡ ከወደ ዳር ተቀምጠው ከነበሩት መካከል አንደኛው ብድግ ብሎ ወደነሱ መጣ ከዮናስ ጋደኛው ጋር ከተጨባበጠ በኃላ ..ቅድም እኮ ከፍላችሁ ሰው ስለበዛ እንካን ደስ ያለህ ብቻ ነው ያልኩህ ለነገሪሩ እዚህ ከመምጣት ሄደህ 30.000 ውን አውጥተህ አትንበሸበሽም .. ይለዋል፡፡
ዮናስም እንደዋዛ ፈገግ ብሎ ..ቢቆይም ምን ችግር ያመጣል ..ይለዋል፡፡ ..እሱስ ልክ ነህ ለነገሩ እኔ አንተን ብሆን በወርቅ ሰሀንም ቢቀርብልኝ ምንም አፒታይት አይኖረኝም ነበር ብሎት ይሄዳል፡፡
እነዮናስ ቦታ መርጠው ከተቀመጡ በኃላ የምግብ ቲኬታቸውን ለአስተናጋጁ ሰጣት ከነሱ ትይዩ ሶስት ጠረጴዛዋች አልፈው አለቃቸውና ጋደኞቹ ተቀምጠዋል የሆነ ወሬ እንደያዙ ከሁኔታቸው ያስታውቃል ፡፡
የአለቃቸው ጋደኛ ለአለቃቸው፡- ምናለ እስቲ መኪና ብታዝለትና ገንዘቡን ቢያመጣ ..ገንዘቡን የት ነው የሚያመጣው ..ብሎ በራሱ አይነት አጠያየቅ መለሰለት ፡፡
..የምልህ - አለው ትንሽ ደንገርገር ብሎት አይ ም ከብሄራዊ ሎተሪ አውጥቶ ማስቀመጥ የሚፈልግበት ቦታ እንዲወስደው መኪና ብታዝለት ..እንደሱ እንካን ጥሩ ሀሳብ ነው አሁን ከሰዐት በኃላ አዝለታለሁ ፡፡
ሁለት ጠና ያሉ ሰዋች በነዮናስ ጠረጰዛ ከመቀመጣቸው በፊት ..ዮናስን እንካን ደስ ያህ ! ቀድም ልንመጣ ስንል ቢሮአችሁ ሰው ሙሉ ነው ስላሉን ነው የተመለስነው ..ብለው ሞቅ ባለ ፈገግታ ጨበጡት ፡፡ ዮናስም ከጣት ጀምሮ በተላበሳት የደከመች ፈገግታው ..አመሰግናለሁ ..! አላቸው፡፡
እነዮናስም የራሳቸው ጨዋታ እየተጨዋወቱ ምሳቸውን ከበሉ በኃላ ለላፍቴሪያው ሲጠጡ የመስርያቤቱን የምግብ ዕቃ ፐርቼዘር ያገኙና እንደ ልመዱ ..እንግዲህ ዮኒ በሬ ክፍት ነው የሚያስፈልግሽን ዕቃ ትነግሪኛለሽ እኔ ነኝ ዕቃ ግዚውን እማከናውንልሽ እ ..ሲከው ዮናስም የወትሮ ቀልድን በቀልድ ለመመለስ ..የ30 ብር ድንችና ቲማቲም ሳይሆን የ30.000 ዕቃ ነው መግዛት የምፈልገው መቼ ላግኝህ ሲለው ..የዛሬ ወር ..ይለዋል ..፡፡ ዣረየ ወርማ መምባሳ ነኝ ለ15 ቀን ያህል ..እንዲያው እኔም ለፔርቼዚንገ ናይሮቢ ስለምሄድ ወደዛው ብቅ ማለቴ አይቀርም ስዚህ እንገናኛለን .. ብሎት እየተሳሳቁ ተላለፉ የወትሮ ቀልዳቸው ነበር ፡፡
እነዮናስም ከምሳ በኃላ ቡና ሻይ ብለው ሲመለሱ ቢሮው ሞቅ ብሎ አገኙት ሐ ዮኒ አለች አንደኛዋ ባልደረባው ሳቅ እፍን እፍን እያደረጋት አንድ ሊስትሮ ሎተሪ እዚህ መስሪያ ቤት መድረሱን ሰምቶ ከኔ ላይ ስለገዙ ጉድ ያመጣ ሁላቸው እኔ ነኝ እና አንድ ሙሉ ልብስ ቢገዙልኝ ብሎ በር ላይ የጠብቅሃል .. አለችው ፡፡
እሱም በዓይኑ ጨረፍ አድርጋት ..ታዲያ አንች ገንዘቡን ሄዶ አላመጣም ነገ ተነገ ወዲያ ይሻላል አትይውምነበር ..ሲላት አረ እራሱ ይሄን ሁሉ አጣርታል ለማንኛውም .. ስሜን በማስታወሻ ቢይዙልኝ ብሎ ነው የምጠብቃቸው .. ብላል ፡፡
ዮናስ በፈገግታ ወደ ወንበሩ አምርቶ ከተቀመጠ በኃላ ..እስቲ ዕዳ ያለባችሁ አንድ በአንድ ንገሪኝ ..አለ እስኪፕሪቶውንና ወረቀቱን አስተካክሎ ይዞ በዚህ ጊዜ ሁሉም ተያዩና አንድ በጀት ክፍል የሚሰራ ከሴቶች ጋር አብሮ የመጣ ቀደም ብል ..እኔ ሶስት ሺህ ብር ዕዳ አለብኝ ..ሲል ሴቶቹ በአይናቸው ገረመሙት ዮናስ እንደቀልድ ፈገግ ብሎ ጻፈና ..ሌላስ ..አለ በጥያቄ መልክ አንደኛዋ ዮኒ እኔ 370.00 ብ አለብኝ አለችው ሌላዋ ለጠቅ አድርጋ 1650 ብር አለብኝ እያሉ የሁሉንም በተራ በተራ ከጻፈ በኃላ ሲደመር 90043.50 ሆነ ፡፡
ይሄን ጊዜ ዮናስ ሎተሪውን ከሸሚዝ ኪሱ አውጥቶ ከብሄራዊ ሎተሪ ደውላ ያረጋገጠችውን ልጅ ጠርታት ይህ ቁጥር ነው 30.000ብር ያስታቀፈኝ ይላታል ፡፡ እሳም አዋን ትላለች ሌሎቹንም ሰብሰብ በሉና ይሄን ቁጥር በማስታወሻ ደብተራችሁ ጻፉት ይላቸውና ሁሉም ከጻፉት በኃላ ከጋደኛው በወሰደው ክብሪት ያቃጥለዋል ፡፡ የተሰበሰቡት ሁሉ መብረቅ እንደመታቸው አይነት ክው ብለው ይቀራሉ ፡፡ ዮናስም ትታቸው ይወጣል ፡፡ ውጪ ያው ቀዝቃዛ አየር ሰውነቱን ሲገርፈው በረዝሙ ተንፍሶ ..አይ የሰው ነገር .. ብሎ የተለመደ ፈገግታውን ለብሶ ቀስ እያለ

No comments:
Post a Comment