ህይወት? ክፍል 4
በመዲናችን አውራ መንገዶች መተላለፊያ ላይ የትራፊክ ህግ እስኪፈቀድላቸው ቆሞ ከሚሎ እግረኞች ወይንም ባለመኪኖች … የዳቦ መግዣ ሣንቲም … እርጥባን የሚለምኑ አንድ ፍሬ ልጆች መታየት ከጀመሩ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው፡፡ ልብሳቸው እላያቸው ላይ ያለቀ፣ ሰውነታቸውን ውሃ ከነካው የሰነበተ፣ የቀኑ የፀሐይ ሐሩር፣ የማታው ብርድና የጠዋቁ ውርጭ ገላቸውን ያደነዘዘው እነኝህ አምቡ ልጆች ገና በዚህ ትንሽ ዕድሜ ለዚህ ሁሉ ፍዳ መዳረጋች ለምን እንደሆነ ለሚጠይቁበት ሩቅ አይሆንም፡፡ ከልመናቸው ባሻገር እርጣባን የሚወረውሩላቸወን ሰዎች፣ ፊት ነሰተው የሚያመናጭቋቸውን አለፍ ሲልም የሚሰድቧቸውን በልጅ ጭንቅላታቸው ቀርፀው የሚይዙት ምናልባትም ከሜችሉት በላይ ይሆናል፡፡
እዛው የመኪና መንገዶች ላይ ከመንገድ ወጣ ባለች አነስተኛ ቦታ ትናንሽ ጎሎች ሠርተው በጨርቅ ኳስ ቀልባቸውን አጥተው የሚጫወቱ ደግሞ እሱ ለዛውም በባዶ እግራቸው፡፡ ጎሎች አካባቢ የት/ቤት ደብተሮች አልፎ አልፎ አይጠራም፡፡ እነኝህ አንድም ከት/ቤት ቀርተው አለበለዚያም የት/ቤት የወር ክፍያ በወቅቁ መክፈል ሳይችሉ የተባረሩ ናቸው፡፡ ወላጆቸው የወር ክፍያውን ከእጅ ወደ አፍ ከሆነች ኑሯቸው ቀናንሰው እስኪከፍሉ ድረስ በመንገድ ዳር ኳስ ጨዋታ ነፍሳቸውን ያስደሰታሉ፡፡ የወር ክፍያ ሳያቋርጡ እየከፈሱና ደህና እየለበሱ በሜማሩት ጓከኞቻቸው በትንሿ ልባቸው እየቀኑ፡፡
ከእነሱ በዕድሜ ብዙም ያልራቁ በቤተሰብ ተጽዕኖ ከትምህርት ሠዓት ውጪ ሊስትሮ፣ ጋዜጦች፣ ሎተሪ እና ሌላም ሸቀጦች ይዞው በአንድ በኩል ቤተሰብ እየደገሙም የሚኖሩ ልጆች ብዙ ናቸው እነዚህ ልጆች ከእንዳንዶች በቀር ት/ቤት የተሰጣቸውን የቤት ሥራዎች በአግባቡ እየሰሩና እያጠኑ ከክፍል ወደ ክፍል የሚሸጋገሩት በጣም ጥቂት ቢሆኑ ነው፡፡
ከዚህ ዕድሜያቸው ትምህርትም ሥራም አቅማቸው የሚፈቅደው አይደለም፡፡ ከትምህርት ሠዓት ውጪ ካልሰሩ ደረቅ ዳቦ እንኳን ሲያረባቸው ነው፡፡ የቤተሰባቸው የኑሮ አቅም ደግሞ አያወላዳም፡፡ ያላቸው ምርጫ እንደምንም ተሯሩጠው መኖር ነው፡፡ የልጅነት ጨዋታ በልጅነት ዕድሜ አያምራቸውም ገና በልጅነታቸው ችግር ብዙ አስተምሯቸዋል፡፡
በታዳጊ ዕድሜ ያለ ሌሎች ደግሞ አሉ ከቤት ወደ ት/ቤት ከት/ቤት ወደ ቤት ቤት እንደደረሱ እረፈት አድርገው፣ የቤት ልብሰ ይቀይራሉ፡፡ መክሰስ አማርጠው ይቀርብላቸውና ከግቢ ሳይወጡ ይጫወታሉ ከጨዋታ በኋላ ወደ ጥናት፡፡ በማግስቱ ቆንጆ የት/ቤት ልብስ ከዘመኑ የልጆ ፋሽን ልብሶቻቸው ለዚያ ቀን ደስ ያላቸውን ለብሰው በሜወዱት የምሳ ዕቃ ምሳቸውን ይዘው ወደ ት/ቤት፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ያለይዋቸው የቪዲዮ ካሴቶች ይመጡላቸዋል፡፡ ከት/ቤት ጓደኞቻቸው ጋር ስልክ ይደዋወላሉ፡፡ የሚሂድባት የቤትሰብ መኪና የትራፊክ መብራት ሲያስቆማት አኒያ የመንገድ ላይ እርጥባን ፈላጊ አንድ ፍሬ ልጆች ወደ መኪና መስተዋት ጣጋ ብለው እጃቸውን ይዘረጋሉ፡፡ መኪና ውስጥ ያሉት የቤት ልጆች አይስክሬም እየላሱ ሲሳሳቁ ለእርጥባን የቆሙት አንድ ፍሬ ልጆች ያዩዋቸዋል፡፡ … አቤት ባርኔጣ እቤት ቀሚስ ደግሞ የሚባሉት ነገር ሲያስጎመጅ … ምራቃቸውን ሲወጡ አባትና እናት የመኪና መስተዋቶችን ግጥም አርገው ዘግተው በዚህ … ደባሪ … የትራፊክ ቀይ መብራት ላይ ኮተር ብለው ያፈጣሉ፡፡ ለእርጣባን የተዘረጉት እጆች መኪናውን መዳበስ ሲጅምሩ ቀዩ መብራት ጠፈፍቶ ቢጫና አረንጓዴ ሲበራ በደመ ነፍስ ወደ መንገድ ዳር ወጣ ይላሉ፡፡ መኪናዋም እኒን ቆንጆ የለበሱ ህጻናትን ይዛ ትፈተለካለች፡፡ እርጣባን ፈላጊዎቹም ዓይናቸው እንደተንከራተተ፣ ዕንባ እንዳቀረረ ሌሎች ተረኛ መኪኖ ይጠብቃሉ፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?
No comments:
Post a Comment